Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ሶፊያን አሙራባትን ከፊዮረንቲና በውሰት ለማስፈረም ስምምነት ላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ሞሮኳዊውን የመሀል ክፍል ተጫዋች ሶፊያን አሙራባት ከፊዮረንቲና በውሰት ለማስፈረም ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ማንቼስተር ዩናይትድ ለጣሊያኑ ክለብ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ የውስት ውል ይከፍላል ነው የተባለው፡፡

ሶፊያን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ታሪካዊ ጉዞ ባደረገው የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ አባል የነበረ ሲሆን በዓለም ዋንጫው ያሳየው ብቃት በስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ዝናን አትርፏል፡፡

የ27 አመቱ የመሀል ክፍል ተጫዋች በዝውውር መስኮቱ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ የመጨረሻ ፈራሚ በመሆን በሚቀጠሉት ቀናት እንግሊዝ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ማንቼስተር ዩናይትድ ቀደም ሲል በተጠናቀቀ ዝውውር ስፔናዊውን ተከላካይ ሰርጂዮ ሬጉሊዬንን ከቶተንሃም ሆትስፐር አስፈርሟል፡፡

ስምምነቱ በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን ሬጉለን ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ልምምድ መስራት መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

በሌላ በኩል የባርሴሎናው አንሱ ፋቲ በውሰት ወደ ብራይተን፣ ክሌመንት ሌንግሌት ከባርሴሎና ወደ አስቶንቪላ፣ ማቲየስ ኑኔዝ ከዎልቭስ ወደ ማንቼስተር ሲቲ፣ ኮል ፓልመር ከሲቲ ወደ ቸልሲ በዛሬው እለት የተጠናቀቁ ዝውውሮች ናቸው፡፡

የክረምት ወር የዝውውር መስኮት ዛሬ ምሽት የሚጠናቀቅ ሲሆን በርካታ ዝውውሮች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.