Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 12፡30 ላይ ይካሄዳል፡፡

በአርሰናል በኩል ቶማስ ፓርቴይ፣ ጁሪየን ቲምበር እና ሞሃመድ ኤልነኒ በጉዳት ምክንያት የማይሰለፉ ሲሆን÷ በአንፃሩ በጉዳት የቆየው ጋብሬል ማጋሌሽ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርግል፡፡

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጉዳት ምክንያት ለወራት ከሜዳ ውጭ የነበሩትን ጋብሬል ጀሱስ እና አሊክሳንደር ዚሸንኮ በዛሬው ጨዋታ የመሰለፍ እድል እንደሚሰጧቸው ተመላክቷል፡፡

በማንቼስተር ዩናይትድ በኩል ተከላካዮቹ ራፋይል ቫራን፣ሉክ ሾው እና ትሬል ማላሲያ በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ሰብስብ ውጭ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በመሃል ክፍል የሚጫወቱት ሜሰን ማውንት፣ኮቢ ሚያኖ እና አማድ ዲያሎ በተመሳሳይ በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፉ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ለአዲሱ ፈራሚ ራሰመስ ሆይለንድ እድል እንደሚሰጡት ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን እርስ እርስ ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል 87 ጊዜ ማሸነፍ ሲችል÷ ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ 101 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡

50 ጨዋታዎችን ደግሞ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ስካይ ስፖርት በዘገባው አስፍሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.