Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለተሰንበት የሴቶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ 4ኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዘገበች

አዲሰ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለተሰንበት ግደይ የሴቶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ 4ኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች፡፡

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በበርሊን ኮንቲነንታል ቱር የሴቶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ ፈጣን ሰዓት ሪከርድን ለመስበር ባትችልም 14 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመግባት ነው 4ኛውን ፈጣን ሰዓቷን ያስመዘገበችው።

በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ አምስት ፈጣን ሰዓቶች የተመዘገቡ ሲሆን ፥ 3ቱ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የተመዘገቡ ናቸው።

የሴቶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ ሪከርድ ፈጣን ሰዓት 14፡05 ሲሆን  ፥ በኬኒያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፒዮጎን መያዙ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.