Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ አቻው ጋር ዘሬ ምሽት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

አስቀድሞ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ያረጋገጠው ብሔራዊ ቡድኑ÷ መርሐ ግብሩን ለማከናነወን ከቀናት በፊት ካይሮ መግባቱ ይታወሳል፡፡

የዋሊያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማሪያም ከጨዋታው አስቀድመው በሰጡት መግለጫ ÷ የብሄራዊ ቡድኑ አባላት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

“ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፍ ባንችልም ÷ ጨዋታው ለቀጣይ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ እና ለቻን ማጣርያ ውድድሮች ራሳችንን የምንፈትሽበት ነው” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ ተጫዋቾች ያላቸውን አቅም እንዲያሳዩ  እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በፈርዖኖቹ በኩል የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ እና የአርሰናሉ ተከላካይ ሞሃመድ ኤልነኒ እንደማይሰለፉ ተገልጿል፡፡

የሁለቱ ታሪካዊ ቡድኖች ጨዋታ በካይሮ አየር ሃይል ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.