Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግብፅ አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በተካሄደው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብፅ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ከግብጽ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በካይሮ አየር ሃይል ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ አድርገዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የግብጽ ብሄራዊ ቡድን ምድቡን በበላይነት አጠናቋል።

በአንጻሩ ዋልያዎቹ የማጣሪያ ውድድራቸውን በአራቱ ተሸንፈው አንድ አቻ በመውጣት እና አንድ ጨዋታ በማሸነፍ በአራት ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.