Fana: At a Speed of Life!

በኒውካስል ግማሽ ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ኒውካስል በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ አሸንፏል፡፡

አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን 59 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር እድሪስ ደግሞ ርቀቱን 1 ሰዓት 01 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በውድድሩ የቤልጂዬሙ አትሌት በሽር አብዲ 2ኛ ሲወጣ÷ ለእንግሊዝ የሚሮጠው ትውልደ ሶማሊያዊው አትሌት ሞ ፋራህ ደግሞ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አትሌት ሞ ፋራህ ይህ ግማሽ ማራቶን ሩጫ የአትሌትነት ዘመኑ የመጨረሻው ውድድር መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.