Fana: At a Speed of Life!

ፍቅረማሪያም ያደሳ በአፍሪካ ዞን የቦክስ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ በፍጻሜ ይጫወታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ቦክሰኛ ፍቅረማሪያም ያደሳ (ጊችሮ ነብሮ) በአፍሪካ ዞን የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ ዛሬ በፍጻሜ ይጫወታል።

ፍቅረማሪያም በዛሬው እለት በ57 ኪሎ ግራም ከናይጀሪያዊው ቦክሰኛ ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን ያደርጋል።

በፍጻሜ ጨዋታው አሸናፊ መሆን ከቻለም ኢትዮጵያን በፓሪሱ ኦሊምፒክ ይወክላል።

በሴኔጋል እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዞን የኦሊምፒክ ማጣሪያ በ57 ኪሎ ግራም ውድድርየአራት ሀገራት ተጋጣሚዎችን አሸንፏል፡፡

ቦክሰኛው የኬንያ ተጋጣሚውን በዝረራ፣ የሊቢያ ተጋጣሚውን በዳኛ ውሳኔ፣ የሞዛምቢክ ተጋጣሚውን በነጥብ  እንዲሁም የአልጀሪያ ተጋጣሚውን በተመሳሳይ በነጥብ በማሸነፍ በውድድሩ ለፍፃሜ ደርሷል፡፡

በመደረኩ አስገራሚ ግስጋሴን ማድረግ የቻለው ፍቅረማሪያም ያደሳ የፍፃሜ ግጥሚያውን ቀን 9 ሰዓት ያደርጋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.