Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ቀን 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያካሂዳል ።

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ÷ 26 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን ከጳጉሜን 3 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያደርግ ቆይቷል።

ከሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋርም የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችሲያደርግ የቆየው ብሄራዊ ቡድኑ÷  ለዛሬው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ማከናወኑ የሚታወስ ነው፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በሁለቱ ሀገራት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ስምምነት መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል መባሉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ ካሸነፉ በቀጣዩ ዙር ከዩጋንዳና አልጄሪያ አሸናፊ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.