ፊፋ የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊፋ የካፍ ዞን የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚሁ የፊፋ ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በካፍ እውቅና ስር ከሚገኙ 50 ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ከዓለም ደግሞ 142ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ሞሮኮ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ፣ሴኔጋል፣ቱኒዝያ፣አልጀሪያ፣እና ግብፅ በቅደም ተከትል ከ2ተኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን፣ሞሪሽየስ፣ቻድ እና ሳኦ ቶሜ ፕሪንሲፔ ከ47ኛ እስከ 50ኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሀገራት መሆናቸውን ከካፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡