ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ሲቲ÷ ፊል ፎደን እና ኤርሊንግ ሃላንድ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡
ሮድሪ በ46ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ክርስታል ፓላስ ከፉል ሃም ያለምንም ግብ እንዲሁም ሉተንታውን እና ዎልቭስ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡