Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው።

ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው የነበረውን ሪከርድ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ሰብራለች፡፡

ባለፈው ዓመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንም 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በመግባት የዓለምን ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡

ከዚያ በፊት በጉዳት ላይ እያለች ባካሄደችው የማራቶን ውድድር የገባችበት ሰዓት 2 ሰዓት ከ34 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ነበር፡፡

ዛሬ ያደረገችው ውድድር የአትሌቷ ሦስተኛ የማራቶን ተሳትፎዋ ነው ሲል ኤን ቢ ሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.