Fana: At a Speed of Life!

በበርሊን የሴቶች ማራቶን ክብረወሰን ለሰበረችው አትሌት ትዕግስት አቀባበል ተደረገላት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ49ኛው የበርሊን ሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ላሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላታል።

አትሌቷ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ስትገባ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውላታል።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የአበባ ጉንጉን ተበርክቷል።

በ49ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2 ሰዓት11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ ውድድሩን በማጠናቀቅ የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን መስበሯ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.