Fana: At a Speed of Life!

በ104 ዓመት ዕድሜያቸው በፓራሹት የዘለሉት አዛውንት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የቺካጎ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ104 ዓመቷ የዕድሜ ባለፀጋ ስማቸውን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲሰፍር በማሰብ ከአውሮፕላን ላይ በፓራሹት መዝለላቸው ተሰምቷል፡፡

ዶርቲ ሆፍነር የተባሉት የዕድሜ ባለፀጋ የፓራሹት ዝላዩን ያደረጉት ከቺካጎ በስተደቡብ ምዕራብ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው አካባቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከአውሮፕላን ላይ ከ 13 ሺህ ጫማ ወይም ከ4 ሺህ 100 ሜትር ከፍታ በፓራሹት በመዝለልም መሬት ከደረሱ በኋላ በስፍራው ለተሰበሰበው ህዝብ ዕድሜ ቁጥር ብቻ ነው ማለታቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ሆፍነር በ100 ዓመታቸውም ተመሳሳይ ሙከራ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

በፓራሹት ዝላይ በፈረንጆቹ ግንቦት 2022 በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ስማቸው የሰፈረው የ103 ዓመቷ ስዊድናዊት የዕድሜ ባለ ፀጋ ሊኔያ ኢንጌጋርድ ላርሰን መሆናቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

አሁን ላይ ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የሆፍነር ዝላይን እንደ ክብረ ወሰን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ስለማስታወቁ ዘገባው አያይዞ ገልጿል።11:41

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.