Fana: At a Speed of Life!

የርገን ክሎፕ የቶተንሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ በድጋሜ እንዲደረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የቶተንሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ በድጋሜ እንዲደረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ክሎፕ ይህን ያሉት በጨዋታው የመስመር አማካዩ ሉዊስ ዲያዝ ያስቆጠረው ጎል በቪዲዮ ረዳት ዳኞች ‘ከጨዋታ ውጭ እንቅስቃሴ አለው’ በሚል ከተሻር በኋላ ነው።

አሰልጣኙ ውሳኔውን ያልተገባ እንደነበርም ገልጸዋል።

በእለቱ ሉዊስ ዲያዝ ሊቨርፑልን መሪ የሚያደርግ ጎል ቢያስቆጥርም ጎሉ በቪዲዮ ረዳት ዳኞች ውሳኔ ከጨዋታ ውጭ መባሉ አግባብ አይደለም የሚልና ውሳኔውን የሚቃወም ሃሳብ ቀርቧል።

ምክንያቱ ደግሞ ሉዊስ ዲያዝ ከጨዋታ ውጭ አለመሆኑን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የወጡ ምስሎች እና የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታ ሃላፊዎች ጎሏ ከጨዋታ ውጭ አለመሆኗን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ይህን ተክትሎም ሊቨርፑል በከርትስ ጆንስ ቀይ ካርድ እና በሉዊስ ዲያዝ ጎል ያልተገባ ውሳኔ በእለቱ ዋና እና ረዳት ዳኞች ላይ ቅሬታውን ሲያቀርብ መቆየቱን ቢቢሲ ስፖርት አስነበቧል።

በዛሬው እለትም የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሰጡት መግለጫ ÷ በቶተንሀም 2 ለ 1 የተጠናቀቀው ጨዋታ እንደገና እንዲካሄድ እፈልጋለሁ ብለዋል።

“ከጨዋታው በኋላ የቀረቡ ማስረጃዎች ዋጋ የላቸውም ያሉት አሰልጣኙ፥ የቫር ውሳኔ ግልፅ ስህተት ነበር፤ ለዚህ መፍትሄ ይሆን ዘንድም ጨዋታው እንደገና መደረግ አለበት” ነው ያሉት።

ይሁን እንጅ ጉዳዩን በተመለከተ የመርሲሳይዱ ክለብ በይፋ ለፕሪሚየር ሊጉ ጥያቄ አለማቅረቡን እና የፕሪሚየር ሊጉ አስተዳዳሪ አካልም ጨዋታው በድጋሜ እንዲካሄድ የማድረግ ፍላጎትን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.