Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች  ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በሳምንቱ በተደረጉ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

በዚህም የሀዋሳ ከተማው ተጫዋች በረከት ሳሙኤል ቡድኑ  ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ  በቀይ ካርድ ከጨዋታ  ውጭ  ሲሆን÷ ለፈፀመው ጥፋት በፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ ፋሲል ከነማ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ  አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ቢጫ ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ ክለቡ 1 ሺህ ብር እንዲከፍል መወሰኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የሻሸመኔ ከተማ ክለብ ቡድን መሪ አቶ ሸምሰዲን ከድር ክለቡ ከከወላይታ ድቻ ጋር በነበረው ጨዋታ በቅድመ ስብሰባ ወቅት ዘግይተው በመምጣታችው ለፈፀሙት ጥፋት የ1 ሺህ ብር የገንዘብ  ቅጣት  ተወስኗል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.