Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና ትዕግስት አሰፋ የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ  ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ፡፡

የአለም አትሌቲክስ የ2023ቱ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት የ11 እጩዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ውድድር የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች አሸናፊዋ እና የዳይመንድ ሊጉ ባለ ሪከርድ ጉዳፍ ፀጋይ እና በበርሊን ማራቶን ሪከርድ በመስበር ያሸነፈችው ትዕግስት አሰፋ በእጩ ዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል፡፡

በእጩነት የቀረቡት አትሌቶች ተመረጡት ከ6 አህጉራት የተወጣጡ ባለሙያዎችን ባቀፈው አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ኤክስፐርቶች ቡድን መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2023ቱ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ድምፅ አሰጣጥ ከተያዘው ሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ የሚደረግ መሆኑን ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.