Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

 

ቀደም ብሎ በተካሄደውና ሀምበሪቾ ዱራሜን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባገናኘው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ 2 ለ 1 አሸንፏል።

 

አቤል ያለው እና አማኑኤል ኤርቦ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ዳግም በቀለ ደግሞ ለሀምበሪቾ ዱራሜ የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆጥሯል።

 

ምሽት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ተገናኝተዋል።

 

ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ሱራፌል ዳኛቸው ለፋሲል እንዲሁም ብሩክ ሙሉጌታ ለኢትዮጵያ መድን ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.