Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሴቶች ከ20 አመት በታች ቡድን ኢኳቶሪያል ጊኒን 4 ለ 1 አሸነፈ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ድል ቀንቷታል።

ከኢኳቶሪያል ጊኒ የተጫወተው የሴቶች ወጣት ቡድን ጨዋታውን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በመጀመሪያው ጨዋታ አንድ አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ የዛሬውን ውጤት ተከትሎ በድምር ውጤት የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 አመት በታች ቡድን 5 ለ 2 አሸናፊ ሆኗል።

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዙር ከማሊ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.