በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን የገጠመው ወላይታ ድቻ በአብነት ደምሴ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡
በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና እና ፋሲል ከነማ ባዳረጉት ጨዋታ ጊት ጋት ጉት በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ ፋሲል ከነማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን በሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ከጣለ በኋላ የመጀመሪያውን ሶስት ነጥብ በ3ኛ ሳምንት ማሳካት ችሏል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!