Fana: At a Speed of Life!

ማንቸስተር ሲቲ ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሜዳው ብራይተንን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

በዚህም ነጥቡን 21 በማድረስ የደረጃ ሰንጠረዡ ለጊዜው እየመራ ይገኛል።

በሌላ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ በርንማውዝን የገጠመው ዎልቭስ በተመሳሳይ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በሜዳው የተጫወተው ኒውካስል ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

ብሬንትፎርድም እንዲሁ በርንሌይን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ሉተን ታውንን ያስተናገደው ኖቲንግሃምፎረስት 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

ቀደም ሲል በተካሄደ የጫወታ መርሃ ግብር በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ሞሀመድ ሳላህ ከእረፍት በኋላ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ኤቨርተንን ማሸነፉ ይታወቃል።

#football

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.