Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሽያ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በግማሽ ማራቶን ውድድሩ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሀጎስ ገብረህይወት እና ሰለሞን ባረጋ ተሳትፈዋል፡፡

በዚህም አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት2ኛ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ 3ኛ እንዲሁም ሰለሞን ባረጋ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኬንያዊው አትሌት ኪቦውት ካንዲ ርቀቱን በ57 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.