Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተዋል፡፡
ፋሲል ከነማ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፍ ችሏል፡፡
ፋሲል ከነማ በውድድር ዓመቱ ነጥቡን ወደ ስምንት ከፍ ሲያደርግ፤ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና ሰባት ነጥቦችን መሰብሰብ ችሏል።
ምሽት 12 ሰዓት ወላይታ ድቻ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.