Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን መንግስት ለአትሌት ደራርቱ ቱሉ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግስት ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠውን የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አበርክቷል፡፡

አትሌት ደራርቱ በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለው የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ላደረገችው አስተዋጽኦ ነው ሽልማት የተበረከተላት፡፡

አትሌት ደራርቱ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሺንዞ አቤ በፈረንጆቹ 2014 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር እንዲወያዩ እድርጋ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2019 ላይም ደራርቱ የጃፓን ስፖርት ኤጀንሲ ኮሚሽነር ከሆኑት ሱዙኪ ዳይቺን እና የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሃላፊ ሃሺሞቶ ሴይኮ ጋር በመምከር የልምድ ልውውጥ ማድረጓ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም አትሌት ደራርቱ ወደ ሃላፊነት ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ የ3 ጊዜ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ የሆነው አትሌት አበበ መኮንን ወደ ጃፓን ካሳማ ከተማ በመሄድ የአትሌቲክስ ስልጠና እንዲሰጥ ማድረጓ ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.