Fana: At a Speed of Life!

አል ኢቲሃድ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተሳታፊው አል ኢቲሃድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናብቷል፡፡

የቀድሞ የቶተንሃም ሆትስፐር እና ወልቭስ አሰልጣኝ የነበሩት ሳንቶስ በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ባሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ ነው ከአሰልጣኝነት የተሰናበቱት፡፡

አሰልጣኙ ከተካሄዱ 12 ጨዋታዎች በ6ቱ ብቻ ያሸነፉ ሲሆን÷ አል ኢቲሃድ ባለፈው ሰኞ በእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ በኢራቁ ኤር ፎርስ ክለብ 2 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡

በዚህም አሰልጣኙ ከስምንት ወራት የሃላፊነት ቆይታ በኋላ አል ኢቲሃድ ጋር በይፋ የተለያዩ ሲሆን ÷ምክትላቸው ሀሰን ካሊፋ ቡድኑን በጊዜያዊነት ይመራሉ ተብሏል፡፡

አል ኢቲሃድ ባለፈው የክረምት ዝውውር መስኮት በርካታ ገንዘቦችን በማውጣት እንደ ካሪም ቤንዜማ፣ንጎሎ ካንቴ፣ፋቢኒሆ እና የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.