የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡
ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነው 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች እሙሽ ዳንኤል እና ንግስት በቀለ አስቆጥረዋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን የፊታችንእሑድ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚያደርግ የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡