Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪነት ሪከርዱን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ምሽት ጎል ማስቆጠሩን ተክትሎ የብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪነት ሪከርዱን 128 አድርሷል፡፡

ሮናልዶ ትናንት ምሽት በዩሮ 2024 ማጣሪያ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 2 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በ46ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ይህን ተክተሎም የ38 ዓመቱ አጥቂ ለፖርቹጋል 204 ጊዜ መሰለፍ የቻለ ሲሆን 128 ጎሎችን በማስቆጠር የብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪነት ሪከርዱን ከፍ ማድረጉን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል፡፡

የአልናስሩ አጥቂ በፈረንጆቹ 2021 በኢራናዊው አጥቂ አሊ ዳኤይ ተይዞ የነበረውን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድን ያሻሻለው ሮናልዶ በትናንትናው ምሽት ጎል ማስቆጠሩ የጎል አስቆጣሪነት ክብረወሰን ከተከታዩ ጋር ያለውን ልዩነት አስፍቷል።

ለብሔራዊ ቡድን በጎል አስቆጣሪነት ሮናልዶ ቀዳሚ ሲሆን ኢራናዊው አጥቂ አሊ ዳኤይ 109 ጎሎችን በማስቆጥር ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ሊዮኔል ሜሲ በ106 ጎሎች ሶሰተኛ፣ ህንዳዊው ሱኒል ኮህቲሪ በ93 ጎሎች አራተኛ ፣ ማሊዥያዊው ሙክታር ዳሃሪ በ89 ጎሎች አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በተሳሳይ በአውሮፓ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ፣ ስፔናዊው ፈረንች ፑሽካሽ ሁለተኛ፣ ፖላንዳዊው ሮቤርቶ ሌዋንዶውስኪ ሶሰተኛ፣ ቤልጂየማዊው ሮሜሎ ሉካኩ አራተኛ እንዲሁም ሃጋሪያዊው ሳንድሮ ኮሲስ አምሰተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.