Fana: At a Speed of Life!

ሌስተር ሲቲ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2022/23 የውድድር ዘመን ሳይጠበቅ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የወረደው ሌስተር ሲቲ በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል።

ቀበሮዎቹ ትናንት ምሽት ሊድስ ዩናይትድ በኪው ፒ አር 4 ለ 0 መረታቱን ተከትሎ ነው ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሯቸው በወረዱበት ዓመት ወደ ሊጉ መመለስ የቻሉት።

በቀጣይ ኢፕስዊች ታዎን ከቀሪ 3 ጨዋታዎቹ 4 ነጥብ የሚያገኝ ከሆነ ከሌስተር ሲቲ በመቀጠል ወደ ሊጉ የሚያድግ ሁለተኛ ክለብ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.