Fana: At a Speed of Life!

ኤቨርተን የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ ህግን ተላልፎ በመገኘቱ 10 ነጥብ ተቀነሰበት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ ህግን ተላልፎ በመገኘቱ 10 ነጥብ ተቀንሶበታል፡፡

ክለቡ በ2021-22 የውድድር ዘመን ከፋይናንስ ጥሰት ጋር በተያያዘ በገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ምርምራ ሲደረግበት መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በተደረገው ማጣራትም በፋይናንሻል ፍትሃዊነት የተቀመጠውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ህግ ተላልፎ የተገኘው ኤቨርተን 10 ነጥብ እንዲቀነስበት ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

በሊጉ የፋይናንስ ህግ መሰረት ክለቦች እንደዚህ አይነት ጥሰት ሲፈፅሙ በሶስት አመት ውስጥ 105 ሚሊየን ፓውንድ እንዲከፍሉ ወይም የነጥብ ቅጣት ይተላለፍባቸዋል፡፡

ኤቨርተን ቅጣቱን በተመለከተ ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳለውም ፕሪሚየር ሊጉ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.