Fana: At a Speed of Life!

በፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ የኦሊምፒክ ውድድር ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ።

ሥምምነቱ የተፈረመው በፓሪሱ አንቶኒ ክፍለከተማ ከሚገኝ ስታዲየም ጋር ነው።

ሥምምነቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ክፍለከተማ ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሶናሌ ናቸው።

በፓሪሱ ኦሊምፒክ በፈረንሳይ እና በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለቡድኑ አቀባበል ለማድረግ እና በውድድሮች ላይ በመገኘት ቡድኑን ለመደገፍ የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎችን ለመስራት ከደጋፊ ተወካዮች ጋር ውይይት መደረጉን የጭው ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውኑ ኦሊምፒክ ቡድኑ አመርቂ ውጤት እንዲያመጣ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.