Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

47ኛው የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ተካሄዷል።

በዚህም የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።

ካሜሮናዊውን ዕጩ በርትራንድ ሜንዱጋ እና ሞሮኳዊውን ሞሐመድ ቦድርን በመብለጥ ነው አቶ ኢያሱ በፕሬዚዳንትነት የተመረጡት።

አቶ ኢያሱ የአፍሪካን ስፖርት በበላይነት በመምራት ከቀድሞ የካፍ ፕሬዚዳንት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በመቀጠል ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል።

በእዩኤል ዘሪሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.