Fana: At a Speed of Life!

23ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 23ኛው ታላቁ ሩጫ ውድድር በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ታላቁ ሩጫ የመዲናዋ ተጨማሪ ድምቀት፣የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ ነው፡፡

ታላቁ ሩጫ የከተማዋን መልካም ገፅታና አብሮነት በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በውድድሩ ዲፕሎማቶች፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የክብር እንግዶች እና በርካታ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል፡፡

ቀደም ሲል የታላቁ ሩጫ ውድድር አካል የሆነው የወንዶች እና የሴቶች ውድድር መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በዚህም በወንዶች ዘርፍ አትሌት ቢኒያም መሃሪ ሲያሸንፍ÷በሴቶች ደግሞ መልክናት ውዱ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.