Fana: At a Speed of Life!

በቱሪዝም ዘርፍ  ዙሪያ ከዓየር መንገዱ ጋር በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚንስትር ዴዔታ ሌንሳ መኮንን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ጋር በቱሪዝም ዘርፍ  ዙሪያ በሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ የጎብኚ ፍሰቱን ለመጨመር በቅንጅት ለመሥራት እና እስከአሁን እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም እንደ “ET-Holiday” ዓይነት የጎብኚ ማበረታቻ መርሐ-ግብሮችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል::

በዓመት ከ 11 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግደው ዓየርመንገዱ÷ ደንበኞቹ ስለኢትዮጵያ የጎብኚ መዳረሻዎች መረጃ እንዲኖራቸውና የተለያዩ የሀገሪቱን አካባቢዎች እንዲጎበኙ ለማድረግ ብሎም አዳዲስ የቱሪዝም ፕሮሞሽን መንገዶችን ለመጠቀም በሚቻልበት አግባብ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.