Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አለም አቀፋዊ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ህዳር 20 ቀን እንደሚጀመር ተገለፀ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ከ6ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መካሄዱን ሲቀጥል የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭትም ያገኛል ተብሏል።

በቀጣይ በሚደረጉ 172 ጨዋታዎች የቀጥታ ሽፋን ለመስጠት ስምምነት መድረሱን የገለጸው የሊጉ አክሲዮን ማህበር ከስምምነቱ ውጭ የሚደረጉ ጨዋታዎችን በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሽፋን ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ለማደረግ እየተነጋገረ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሊጉ ነገ ጅማሮውን ሲያደርግ ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ሀምበሪቾ ዱራሜ ከፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ13 ነጥብ በግብ ክፍያ ሲመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ11 መቻል ደግሞ በ10 ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.