Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማን ያገናኛኘው የወንድማማቾች ደርቢ ባዶ ለባዶ በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው የ24ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ተመጣጣኝ የጨዋታ እንቅስቃሴን አስተናግዷል።

ክለቦቹ በሊጉ 10 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ 7 ጊዜ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ውጤት ተከትሎ ባህርዳር ከተማ ነጥቡን ወደ 41 ከፍ በማድረግ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፋሲል ከነማ በ37 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የ24ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.