Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ባሕርዳር ከተማ ድል ቀናው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ባሕዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

9፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ለባሕዳር ከተማ ፍራኦል መንግሥቱ እና ቸርነት ጉግሳ እንዲሁም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ አማኑኤል ተርፉ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ሞሰስ አዶ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 11 በማድረስ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ13 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ነው፡፡

የ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ- ግብር ሲቀጥል÷ ምሽት 12፡00 ላይ ሲዳማ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

12፡00 ላይ በተደረገ የጨዋታ መርሐ-ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና ያለግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና በ4 ነጥብ 11ኛ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና 3 ነጥቦችን በመያዝ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.