Fana: At a Speed of Life!

በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶቹ አትሌት ሲሳይ ለማ ርቀቱን 2 ሰአት ከ1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል፡፡

ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው ቀነኒሳ በቀለ 2:04:19 በመግባት ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቋል፡፡

በሴቶች ደግሞ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ፣ አልማዝ አያና እና ህይወት ገብረኪዳን ተከታትለው በመግባት ከ1ኛ እስከ 2ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.