Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

9 ሰዓት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሀምበርቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የወልቂጤ ከተማ ግብን አሜ መሐመድ ያስቆጠረ ሲሆን÷በዚህም ቡድኑ ተከታታይ ድልን አሳክቷል።

እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለወላይታ ድቻ የማሸነፊያ ሁለት ጎሎችን ቢኒያም ፍቅሬ እና ዘላለም አባቴ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.