Fana: At a Speed of Life!

ለኢንተርናሽናል ዳኝነት የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢንተርናሽናል ዳኝነት የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡

በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ በወንዶች ሰባት ዋና እና ሰባት ረዳት እንዲሁም በሴቶች አራት ዋና እና አራት ረዳት ዳኞች ተመርጠው ለፊፋ ዳኞች ኮሚቴ መላካቸው ይታወቃል።

የዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበርም ከአንድ ወንድ ረዳት ዳኛ ውጭ ሌሎች እጩ ዳኞች ለኢንተርናሽናል ዳኝነት እንደተመረጡ ማስታወቁን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-

በወንድ ዋና ዳኝነት፡- ባምላክ ተሰማ፣ ሃይለየሱስ ባዘዘው፣ በላይ ታደሰ፣ ቴዎድሮስ ምትኩ፣ አሸብር ሰቦቃ፣ ማኑሄ ወልደጻዲቅ እና ኤፍሬም ደበሌ

በወንድ ረዳት ዳኝነት፡- ትግሌ ግዛው፣ ተመስገን ሳሙኤል፣ ፋሲካ የኋላሸት፣ ይበቃል ደሳለኝ፣ ሙስጠፋ መኪ እና አሸብር ታፈሰ

በሴቶች ዋና ዳኝነት ፡- ጸሃይነሽ አበበ፣ መዳብ ወንድሙ፣ ሲሳይ ራያ እና ማርታ መለሰ

በሴቶች ረዳት ዳኝነት ፡- ወይንሸት አበራ፣ ወጋየሁ ዘውዱ፣ ይልፋሽዋ አየለ እና ብቱካን ማሞ መመረጣቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.