Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሀድያ ሆሳዕና እና ባህር ዳር ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
 
ከሰአት በኋላ በተካሄደ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ከፋሲል ከነማ ተገናኝተው ሀድያ ሆሳዕና 2 ለ 1 አሸንፏል።
 
ተመስገን ብርሃኑ እና ግርማ በቀለ ለሀድያ ሆሳዕና የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ፍቃዱ አለሙ ደግሞ ለፋሲል ከነማ የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆጥሯል።
 
ማምሻውን በተካሄደ ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል።
 
ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የተጫወተው ባህር ዳር ከተማ ጨዋታውን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።
 
ፍራኦል መንግስቱ እና ያሬድ ባየህ ለባህር ዳር ከተማ የድል ጎሎቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
 
የድሬዳዋ ከተማን ማስተዛዘኛ ጎልም ያሬድ ባየህ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.