Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲና ኒውካስል ዩናይትድ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየም ሊግ በሜዳቸው የተጫወቱት ቼልሲና ኒውካስል ዩናይትድ ድል ቀናቸው።

በሜዳው ሼፊልድ ዩናይትድን ያስተናገደው ቼልሲ በፓልመርና መጃክሰን አማካኝነት በ54ኛውና በ61ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏን።

ፉልሃምን ያስተናገደው ኒውካስል ዩናይትድ 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ሚለይ፣ አልሜሮን እና በርን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በተመሳሳይ በሜዳው ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ በ24ኛውና በ54ኛው ደቂቃ ላይ በግሪሊሽና ሌዊስ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም ክሪስታል ፓላስን ማቴታ በ76ኛው ደቂቃ እንዲሁም በጭማሪ ሰዓት ኦሊሴ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠው ግብ 2 ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.