Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ብራይተንን በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል ብራይተንን 2 ለ 0 በማሸነፍ ፕሪሚየር ሊጉን በጊዜያዊነት ከሊቨርፑል ተረክቦ መምራት ጀምሯል፡፡

በኤሚሬትስ ስታዲየም ብራይተንን ያስተናገዱት መድፈኞቹ በጋብሬል ጄሱስ እና ካይ ሀቨርትዝ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም÷ መድፈኞቹ ነጥባቸውን 39 በማድረስ የፕሪሚርሊጉን መሪነት በጊዜያዊነት ከሊቨርፑል ተረክበዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ  ዌስትሃም ዎልቭስን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ የኡናይ ኤሚሬው ቡድን አስቶንቪላ ከመመራት ተነስቶ 2 ለ 1 በማሸነፍ በ38 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

 

የሊጉ መርሐ-ግብር ሲቀጥሉ ሊቨርፑልን ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያገናኘው የሣምንቱ ታላቅ ጨዋታ ምሽት 1፡ 30 ላይ በአንፊልድ ይደረጋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.