Fana: At a Speed of Life!

በጥሎ ማለፉ ናፖሊ ከባርሴሎና  እንዲሁም ላዚዮ ከባየርን ሙኒክ ተገናኝተዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆኗል።

በድልድሉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በጠንካራ አቋሙ የዘለቀው አርሰናል ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር ተገናኝቷል።

በአንጻራዊነት ጠንካራ በሚመስለው ድልድል የጣሊያኑ ናፖሊ ከስፔኑ ባርሴሎና  እንዲሁም ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ላዚዮ ከጀርመኑ ሃያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ጋር ተገናኝተዋል።

የፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ከስፔኑ ሪያል ሶሲየዳድ እንዲሁም ኢንተርሚላን ከዲያጎ ሲሚዮኒው አትሌቲኮ ማድሪድ  ጋር ይጫወታሉ።

የሆላንዱ ፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ሲጫወት ማንቼስተር ዩናይትድን ጥሎ ያለፈው የዴንማርኩ ኮፐንሀገን ደግሞ ከጋርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር በጥሎ ማለፉ የሚጫወት ይሆናል።

የጀርመኑ አር ቢ ሌፕዚግ ደግሞ ከቻምፒየንስ ሊጉ ባለ ክብረወሰን ሪያል ማድሪድ ጋር ተገናኝቷል።

የጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ጨዋታዎች በየካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት እና የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ በወሩ መጨረሻ ይደረጋሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.