Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ 8ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮው ውድድር ዓመት ስምንተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

በለንደን ስታዲየም ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የተጫወተው ማንቼስተር ዩናይትድ ጃሬድ ቦዌን እና ሞሃመድ ኩዱስ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን በ18 ጨዋታ 28 ነጥቦችን ሰብሰቦ በነበረበት 8ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ሲገደድ በዛሬው ጨዋታ ድል የቀናቸው መዶሻዎቹ በ30 ነጥቦች ደረጃቸውን ወደ 6ኛ ከፍ አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.