Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም ድል ሲቀናው ኒውካስትል በሉተን ተሸንፏል

 

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 13 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሓ ግብር ማምሻውን አራት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

12 ሰአት ላይ በተካሄዱ ጨዋታዎች በርንሌይ እና ሉተን ታዎን ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግበዋል።

ወደ ክራቨን ኮቴጅ በማምራት ከፉልሃም ጋር የተጫወተው በርንሌይ ጨዋታውን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ኦዶበርት እና በርግ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድን ያስተናገደው ሉተን ታዎን ደግሞ በአንዲ ቶውሴንድ ጎል የ1 ለ 0 ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል።

አሰልጣኝ ስቲቭ ኩፐርን በአሰልጣኝ ኑኖ ኢስፒሪቶ የተካው ኖቲንግሃም ፎረስት ከበርንማውዝ ጋር በሜዳው ተጫውቶ በጭማሪ ሰአት በተቆጠረበት ጎል ተሸንፏል።

ጨዋታው 3 ለ 2 ሲጠናቀቅ ዶሚኒክ ሶላንኬ ለበርንማውዝ ሶስቱንም ጎሎች በማሰቆጠር ሐት-ትሪክ ሰርቷል።

ኢላንጋ እና ውድ ደግሞ ለኖቲንግሃም ጎሎቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

በሜዳው ጥሩ መነቃቃት እያሳየ ያለውን የሼን ዳይሹን ኤቨርተንን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሪቻርሊሰን እና በሶን ጎል 2 ለ 1 አሸንፎ ወጥቷል።

ኤቨርተን ከሽንፈት ያልታደገውን የማስተዛዘኛ ጎል በአንድሬ ጎሜስ አማካኝነት አስቆጥሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.