Fana: At a Speed of Life!

ሰር ጂም ራትክሊፍ የማንቼስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ ገዙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ የማንቼስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ መግዛታቸው ተገልጿል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድን በ790 ሚሊየን ዩሮ የገዙት የግሌዘር ቤተሰቦች ከ13 ወራት በፊት የክለቡን ድርሻ ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም እንግሊዛዊው ቢሊየነር የክለቡን 25 በመቶ ድርሻ መግዛታቸው የተገለፀ ሲሆን ኢኔዮስ ግሩፕ የራትክሊፍ ኩባንያ የማንቼስተር ዩናይትድን የአስተዳደር ስራዎች ይረከባል ነው የተባለው፡፡

የ71 ዓመቱ ቢሊየነር የክለቡ አስተዳደር ስራዎችን ለማዘመን ከ300 ሚሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ እንደሚያደርጉ ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

የማንቼስተር ከተማ ተወላጅ እና የማንቼሰተር ዩናይትድ ቀንደኛ ደጋፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቢሊየነሩ  ክለቡ ያለበትን አስተዳደራዊ ቀውሶች እንደሚያሻሽሉ እምነት ተጥሎባቸዋል፡፡

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ከፈረንጆቹ 2013 ወዲህ የፕሪሚየርሊጉን ዋንጫ ማንሳት ያልቻለ ሲሆን ከክለቡ ውጤት ማጣት ጋር ተያይዞ አሜሪካውያኑ የግሌዘር ቤተሰቦች ከክለቡ ደጋፊዎች ትችት እያስተናገዱ ይገኛል።

ደጋፊዎቹ “አሜሪካውያኑ ባለሃብቶች ለክለቡ ሳይሆን ትርፋቻወን ብቻ የሚያስቡ ናቸው” በማለት ክለቡን እንዲሸጡ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ።

ከዚህ ቀደም ኳታራዊው ቢሊየነር ሼክ ጃሲም ቢን ሃማድ አል ታኒ ክለቡን ለመግዛት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ቢያቀርቡም አሜሪካውያኑ ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ቢሊየነሩ በተደጋጋሚ ያቀረቡትን የግዢ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎም ክለቡን የመግዛታ ሃሳባቸውን ውድቅ ማድረጋቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.