Fana: At a Speed of Life!

ጥንዶቹ ቀሪ ዘመናቸውን በባህር ላይ ለመቅዘፍ ንብረታቸውን ሸጠዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍሎሪዳ ነዋሪ የሆኑት ጥንዶች ከሦስት ዓመታት በፊት ያላቸውን ንብረት ሁሉ በመሸጥ በመርከብ ዓለምን ለመዞር መወሰናቸውን ተናግረዋል።
 
ጥንዶቹ ንብረታቸውን ከሸጡ በኋላ የሞተር ቤት ገዝተው የነበረ ቢሆንም የ76 ዓመቱ ጆን ማሽከርከር እንደሰለቸው ሚስት ሜሎዲ ይናገራሉ፡፡
 
በዚህ መሀል በፌስቡክ ከሮያል ካሪቢያን ጋር ለ274 ቀናት የሽርሽር የጉዞ ማስታወቂያ እንደተመለከቱ እና በባህር ላይ ቋሚ የህይወት ጉዞ መጀመራቸውን ይገልፃሉ።
 
ጥንዶቹ አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ እና ደቡብ ፓሲፊክን ጨምሮ የረጅም ጊዜ ተከታታይ የባህር ቀዘፋ አካል በሆነው በዶሚኒካን ሪፐብሊክ እየተንሸራሸሩ ይገኛሉ።
 
አዲሱ ህይወታቸው አስደሳች እንደሆነ የሚናገሩት ጥንዶቹ የዋጋው ርካሽ መሆን ደግሞ ይበልጥ ተወዳጅ እንዳደረገው ተናግረዋል።
 
ወደ ባህር ዳርቻው ሲሄዱ የስልክ፣ የመርከብ እና ከጥቂት የዱቤ አገልግሎት ክፍያ ደረሰኞች በስተቀር ሌላ ደረሰኝ እንደሌለባቸው ጆን ይናገራሉ።
 
ከእንግዲህ የቤት ማስያዣም ሆነ የቤቶች ወጪ፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ፣ የንብረት ኢንሹራንስ ወይም የፍጆታ ክፍያዎች እንደማያስጨንቋቸውም ያብራራሉ፡፡
 
የባህር ላይ ህይወታቸው በየብስ ላይ ሲኖሩ በነበሩበት ጊዜ ከነበረው ወጪ በግማሽ ያህል ወጪ እንደሚቀንስም ነው የሚናገሩት።
ሜሎዲ እና ጆን በመርከብ ላይ ትልቁ ችግራቸው አብዝቶ መብላትና መጠጣት እንደሆነ ይገልፃሉ።
 
ይሁንና ይህንን ለማስተካከል በመርከቧ ላይ በተቻለ መጠን ለመዟዟር እንደሚሞክሩ እና በወደብ በሚኖራቸው ቆይታ በቀን ወደ ስምንት ኪሎ ሜትሮችን በእግር እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰዋል።
 
መርከቧ በወደቦች ከሶስት እስከ አምስት ቀናት እንደምትቆም የገለፁት ጥንዶቹ÷ ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ከፈለጉም እንደሚችሉና ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.