Fana: At a Speed of Life!

ዋይኒ ሩኒ ከበርሚንግሃም አሰልጣኘነቱ ተሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ በርሚንግሃም ሲቲ ዋይኒ ሩኒን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ።

በእንግሊዝ ቻምፒዮን ሺፕ እየተሳተፈ የሚገኘው በርሚንግሃም ሩኒን ባለፈው ጥቅምት ወር በዋና አሰልጣኝነት መቅጠሩ ይታወሳል።

አሁን ላይ ክለቡ የገባበትን የውጤት ቀውስ ተከትሎም የ38 አመቱን የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ እና እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታውቋል።

ሩኒ ክለቡን ተረክቦ በአሰልጣኝነት ከመራባቸው 15 ጨዋታዎች ውስጥ በርሚንግሃም በዘጠኙ መሸነፉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።

ክለቡ ከሩኒ በፊት ከነበረበት 6ኛ ደረጃ ወርዶ አሁን ላይ 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የተጫዋቾች ብቃት አሰልጣኙ ስቲቭ ስፑነርም ክለቡን በጊዜያዊነት ይረከቡታል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.