Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 27 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀምበሪቾ ዱራሜን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ባሲሩ ኡመር እና በረከት ግዛው ናቸው ያስቆጠሩት፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ወላይታ ድቻ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች ቢንያም ፍቅሩ እና አብነት ደምሴ ሲያስቆጥሩ ÷ የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ አቡበከር ሳኒ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.