Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ኢራን በራሳቸው ገንዘብ በቀጥታ ለመገበያየት ወሰኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ኢራን በአውሮፓው “ስዊፍት” በኩል ሲያደርጉ የነበረውን ግብይት ትተው በራሳቸው ገንዘብ በቀጥታ ሊገበያዩ መወሰናቸው ተነገረ፡፡

ሀገራቱ በቀጥታ በራሳችን ገንዘብ መገበያየት እየቻልን ለምን የዶላርና ዩሮ ምንዛሬ እንጠብቃለን ማለታቸውን ፋርስ የዜና አገልግሎት መዘገቡም ተጠቁሟል፡፡

የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ምክትል ኃላፊ ሞህሰን ካሪሚ እንዳሉት፥ ሀገራቱ ወጪ እና ገቢ ንግዳቸውን በቀጥታ በባንኮቻቸው በኩል በተዘረጋ ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ከዚህ በኋላ በእጅ አዙር ለመገበያየት አውሮፓን አይፈልጉም መባሉን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ኢራን ወደ ሩሲያ የምትልከውን የወጪ ንግድ ገቢ በሀገሯ መገበያያ ገንዘብ ሪያል እንደምትቀበልና ሩሲያም ግብይቷን በሩብል እንደምትፈፅም ተነግሯል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ቁልፍ የተባሉ ባንኮቿ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ልውውጥ እና መላላኪያ ሥርዓት መውጣታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

መሠረቱን ቤልጂየም ያደረገው “ስዊፍት” ዓለም አቀፍ የገንዘብ መለዋወጫ እና መላላኪያ ሥርዓት ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.