Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

የሻሸመኔ ከተማን ግብ አብዱልቃድር ናስር ሲያስቆጥር÷ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገችዋን ግብ ደግሞ ራምኬል ጀምስ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማን ያገናኘው ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.